በዋጋ ግሽበት ላይ እውቀት ያላችሁ ከቻላችሁ አስረዱኝ።
ያለኝ መሰረታው እውቀት እንደሚከተለው ነው።
የዋጋ ግሽበት መነሻው የአቅርቦት እና የፍላጎት አለመጣጣም እንደሆነ እረዳለሁ። ይህ ማለት በገበያ ላይ ብዙ የሚዘዋወር ገንዘብ ነገር ግን ትንሽ የእቃ/ምርት አቅርቦት ሲኖር ማለት ነው። በገበያ ውስጥ የሚዘዋወር ገንዘብ እንዲኖር ደግሞ በሰው እጅ በቂ ገንዘብ መኖር አለበት። ለዚህ ደግሞ በቂ የወረቀት ገንዘብ ታትሟል ማለት ነው።
-
- ጥያቄዬ እዚህ ላይ ነው። ተመጣጣኝ አቅርቦት በሌለበት ሁኔታ ለምንድነው ካለው አቅርቦት በላይ ገንዘብ የሚታተመው?
ቤላ ገንዘብ ስለታተመ ብቻ አይደለም ከአቅርቦት በላይ በገበያው የሚዘዋወረው።
ኢኮኖሚው ጥሩ በነበረበት ወቅት የታተመው ገንዘብ በገበያ እንዳለ መሆኑን አትዘንጊ።
ምናልባት ያንን የታተመ ገንዘብ ኢኮኖሚውን ለማመጣጠን ከገበያ ሰብስቦ ማስወገድ ነው ሚሻለው ወይስ በገበያው ያለውን ገንዘብ የመግዛት አቅም ማዳከም። እሱ የምርጫ ጉዳይ የሚሆን ይመስለኛል።
ቤላ ይኼ ጥያቄ ካቅሜ በላይ ነው። ማተሚያ ቤቱ ስራ እንዳይፈታ ይሆናል። 😉