ከላይ በርዕሱ እንደተጠቀሰው የፈረሰ ቤት መገለጫው ምንድነው?
Share
Lost your password? Please enter your email address. You will receive a link and will create a new password via email.
Please briefly explain why you feel this question should be reported.
Please briefly explain why you feel this answer should be reported.
Please briefly explain why you feel this user should be reported.
የፈረሰ ቤት መገለጫው ፦ ግርግዳና ጣሪያ ያለው ከሆነ፦ ግርግዳና ጣሪያው ይፈርሳል፥ ይወድቃል። ነዋሪዎቹን ከዝናብ፥ ከነፋስ፥ ከብርድ እና ከመሳሰሉት መከላከል ስለማይችል፥ ነዋሪዎቹ ጥለውት ይኼዳሉ።
ግርግዳና ጣሪያው ከመውደቁ በፊት በርካታ ባህሪያትን ያሳያል። መግባባት እይቻለም፣ ተገደህ እንጂ ፈቅደህ እና ወደህ ስለማትኖር ግርግዳውን እንደ ፍልፈል እራስህ ሰርስረህ ታፈርሰዋለህ።
የፈረሰ ቤት አንዱ መገለጫው እራስ ወዳድነት። እራሱን የሚወድ ለሌላው ግድ የሌለው፣ የሌላው ጭንቀትም ሆነ ሀዘን ግድ የማይለው። የሌላው ማግኘት የማያስደስተው እንዲህ እንዲህ እያሉ ብዙ መዘርዘር ይቻላል።
የፈረሰ ቤት መገለጫው ነዋሪዎቹ ድርሻቸውን ለመካፈል ፍርድ ቤት ሲመላለሱ ወይም በየፊናቹው ጠበቃ ሲፈልጉ ካየህ ያው ቤቱ ፈርሷል ማለት ነው።
ዳኛው በሽማግሌ መፍታት የምትችሉት ከሆነ ብሎ ሽማግሌ ፈልጉ ይላል። ሽማግሌውም የናንተን ጉዳይ በማየቴ ምንድነው ድርሻዬ ይላል። መፍትሄ ሁሉ ድርሻውን ፈላጊ ነው።
የፈረሰ ቤት ቀላዋጭ፣ ወሬኛ እና ቅዠታም ይበዛዋል።