እንደልማድ አብዛኛው ሰርግ በኢትዮጵያ የሚሰረገው በጥር ወር ለምን ሆነ? በተለይ ቀደም ባለው ግዜ ጥር ወር የሰርግ እና ምላሽ ወር ነበር። ምክኒያት ይኖረው ይሆን?
Share
Lost your password? Please enter your email address. You will receive a link and will create a new password via email.
Please briefly explain why you feel this question should be reported.
Please briefly explain why you feel this answer should be reported.
Please briefly explain why you feel this user should be reported.
ከ 13ቱ ወራቶች በተለየ ጥር ወር ለጋብቻ የሚመረጥበት ብዙ ምክኒያቶች ይኖሩት ይሆናል።
ኅዳር የታጨደ እስከ ታኅሳስ አጋማሽ ድረስ ተወቅቶ ጎተራ ይገባል። ጥር ላይ ጎተራ ሙሉ ነው። ተድላ ደስታ ለማድረግ ይመቻል።
በተጨማሪም ሀይማኖታዊ ማብራሪያ ይኖረው ይሆናል። ጥር ላይ ወሩን ሁሉ ሀይማኖታዊ ክብረ በዐል አለ። ምናልባት ጥንዶችን ለማጣመር ከሌሎቹ ወራት በተለየ ምቹ ጊዜ ይሆናል።
ጥምቀት በጥር ወር ነው አይደል? የቃና ዘገሊላ ሰርግ በዚህ ወቅት ከመሆኑ ጋር ዝምድና ይኖረው ይሆን? መላ ምት ነው።
የጥር ትዳር “የአብርሃም እና የሳራ” ይሆናል ተብሎ በተለምዶ ስለሚታመን ነው።