በሳልነት ከእድሜ እና ትምህርት ብቻ የሚገኝ ሳይሆን በልምድ የሚገኝ የአመለካከት ለውጥ ነው። በሳል ሰው ባሕሪያት በጥቂቱ
- ብቻውን መሆን የሚመቸው፦በሳል ሰው ሁል ጊዜ ጓደኛ ወይም ሌላ ሰው በዙሪያው እንዲኖር አይሻም
- ልዩነትን መቀበል የሚችል፦ሌላው እንደእሱ እንዲያስብ ወይም እንዲያደርግ የማይጠብቅ። እያንዳንዱ ልዩ መሆኑን ዩሚቀበል።
- የራሱን የሒወት ጎዳና መምረጥ የሚችል
- ሌላውን በአክብሮት የሚያስተናገድ
- ሀላፊነት የሚሰማው፦ ለውድቀት ሌላውን ተጠያቂ የማያደርግ።
- ከማውራት ይልቅ የሚያዳምጥ
- ነገሮችን ለግል ጥቅሙ እንደሚመቸው የማይሸርብ
- ደስታውን በቁስ ሳይሆን ዛሬ ላይ ባለው የሚያጣጥም
ጨምሩበት?