ቡና በቀን ቢያንስ ሶስቴ እጠጣለሁ። ጠዋት እንደነቃሁ በባዶ ሆዴ፣ ረፈድ ሲል እና ማታ ከመተኛቴ በፊት። እነዚህ የማይቀሩ ናቸው። በመካከል ባገኘሁት አጋጣሚ ቡናን በቃኝ ማለት አልችልም። ከዓመት በፊት የጠዋቱን እና የማታውን እርግፍ አርጌ ተውኩ። ሌላውን ሰአት እጠጣለሁ። ኪሎየ የጠዋት እና ማታ ቡና መጠጣት ካቆምኩ ወደ 13 ኪሎ ጨመርኩ። ቡና መጠጣት ከክብደት እና ከጤና ጋር ይገናኛል?
Share
የሱስ ጠቃሚ ስራ ብቻ ነው። አሱም ሲበዛ አካላዊ ጉዳት ያመጣል።
በባዶ ሆድህ ቡና መጠጣትህ ምናልባት ቁርስ እንዳትበላ ቆልፎህ ይሆናል። የኼም በሂደት የሰውነት መጎዳት፤ መክሳት ወይም ክብደት መቀነስ አስከትሎብህ ይሆናል።
ቡናውን ስታቆም ቁርስ በአግባቡ መብላት ስትጀምር፤ ሰውነትህም በካፊን ከመወጠር በማረፉ በቂ እንቅልፍ እያገኘህ ይሆናል። ሰውነትህም እራሱን መጠገን ጀምሮ ይሆናል። ውፍረትህ ከቁጥጥር ውጪ እንዳይሆን ጠብቀው።
በተረፈ ጤነኛ እስከሆንክ ድረስ የሚያሳስብ ነገር የለም። የሚያሳስብ ነገር ካለ ሐኪም ማማከር ነው።