ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል የሚለው ተረት እና ምሳሌ ምን ለማለት የተነገረ ነው? ሹማምንትን ለሌብነት እና ለስርቆት ለማበረታታት የተነገረ ይሆን? ስርቆትን የሚያበረታታ ማኅበረሰብ ነበር ማለት ነው?
Share
Lost your password? Please enter your email address. You will receive a link and will create a new password via email.
Please briefly explain why you feel this question should be reported.
Please briefly explain why you feel this answer should be reported.
Please briefly explain why you feel this user should be reported.
እንደተርጓሚው ነው። ሆዳም የሆነ እና ለሌብነቱ ማጣቀሻ የፈለገ ሲተረጉመው ፦ ሲሾም ያልሰረቀ ሲሻር ይቆጨዋል ለማለት የተነገረ ይመስለዋል።
ሌብነትን ተጠያፊ ማኅበረሰብ ፥ ሃብት የሃጢእት ስር የሚመስለው ሲተረጉመው ፥ መብላት መጠጣት ማለት የስራ እቅዱን ማሳካት የሹመት ሀላፊነቱን መወጣት ነው ብሎ ስለሚያስብ ። የሹመት ዘመኑ ሲያበቃ ይኼን ሳላደርግ ብሎ እንዳይቆጨው። ይህ ማኀበረሰብ ሲተረጉመው፦ ሲሾም ያልሰራ ሲሻር ይቆጨዋል ብሎ ይተረጉመዋል።
ይህ ተረትና ምሳሌ በተነገረበት ወቅት ሌብነት ይቅርና የሌላን መመኘት ጸያፍ የሆነበት ጊዜ ይኆናል። በሙስና የሰከረ ሲተረጉመው ያው ሌብነቱ በአበባል ተመርቆ የተሰጠኝ ነው እያለ እራሱን ለማጽናናት ያሰበ ይሆናል።