ከአመታት በፊት ወደሰሜን ተራሮች በቡድን በሄድንበት ጊዜ፤ ዋልያ እና ጭላዳ ዝንጀሮን ለማየት ችለን ነበር። ቀይ ቀበሮን ወደ ባሌ ሄደን ለማየት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካልንም። እንጣጥ፣ እንጣጥ እያሉ አየር ላይ ተንሳፍፈው ወደምድር እየተመለሱ የሚጫወቱ አጋዘን፣ የወንድዬው አጋዘን ቀንዱ ከሰውነቱ የሚረዝም ይመስላል። የሜዳ አህያ፣ የተለያዩ ወፎችን እና በጣም አስደናቂ የሆነ በዛፍ የተሞላ ጫካ እና ለከተማዋ ስም መጠሪያ የሆነውን አርባ ምንጮችን፤ አርባ ምንጭ ሄደን ተመለከትን። ደስ የሚል ጊዜ ነበር። ፎቶ ማጋራት ቢቻል ኖሮ የተወሰኑ ፎቶዎችን አጋራችሁ ነበር።
ከላይ የጠቀስኳቸው ሁሉ ብርቅዬ ናቸው እያልኩ አይደለም። ከዋሊያ፣ ከጭላዳ ዝንጀሮ እና ከቀይ ቀበሮ ውጪ ሌሎች ብርቅዬ እንስሳት እና አእዋፋት በኢትዮጵያ ይገኛሉ ብዬ አስባለሁ። መገኛቸው የት ነው? የት ብንሄድ እናያቸዋለን? የቅርብ ግዜ ጽሁፍ ሳነብ አውራሪስ በኢትዮጵያ ወደ ጅንካ አካባቢ ይገኝ እንደነበር እና አሁን ግን ሸሽቶ ወደኬኒያ እንደገባ እና ኢትዮጵያ ውስጥ አውራሪስን ማየት እንደማይቻልይ ይጠቁማል? እንደዚህ የጠፉ ወይም የተሰደዱ እንስሳት ይኖሩ ይሆን?
ጥቁር አንበሳ ፦ ባሌ መገኛው
ጥቁር አውራሪስ፦ አዋሽ ስምጥ ሸሎቆ የነበረ ወደ ኦሞ ወንዝ የሸሸ በመጨረሻም ከኢትዮጵያ የጠፋ ይመስለኛል
ዝሆን፦ ጅንካ እና ኦሞ አካባቢ የሚገኝ።
የወፍ እና የአይጥ ዘር ቆጥረህ አትጨርስም።
ጥንዚዛ፦ አሁን አለ ይሆን ጥቁር ከንብ ሰባት እጥፍ ገዘፍ ያለ።
ትኋን፥ በማላታይን ገድለን ለመጨረስ የታገልን
መዥገር
ቁንጫ
እነዚህ ከኢትዮጵያ ውጪ ሌላ ቦታ ይኖሩ ይሆን