ጠንካራ አስተዳደር መለኪያው ምንድነው? አስተዳደር ስንል ቤት፣ ድርጅት ወይም አገርን ማስተዳደር ሊሆን ይችላል።
Share
Lost your password? Please enter your email address. You will receive a link and will create a new password via email.
Please briefly explain why you feel this question should be reported.
Please briefly explain why you feel this answer should be reported.
Please briefly explain why you feel this user should be reported.
ጠንካራ አስተዳደር ከራሱ በላይ የሆነ ስርዐት ይገነባል። ምሳሌ ጃንሆይ – ቀኃሥ፥ ከስልጣን ቢወርዱም ጠንካራ አስተዳደር ስለነበረ ኢትዮጵያ ቀጠለች። እሳቸው ኖሩም አልኖሩም አገሪቷ እንዳለች ቀጠለች።
መንግስቱ ከስልጣን ወረደ ፥ ኤርትራ ተገነጠለች። ከራሱ የበለጠ አስተዳደር ስላልነበረ ኤርትራ ተገነጠለች፥ ኢትዮጵያም ተቆረሰች። መንግስቱ ሲሄድ ኤርትራ ሄደች።
የወያኔ ኢህአዴግ አስተዳደር እንደምታየው ነው። ህወሓት ከስልጣን ሲወርድ፣ ምስቅልቅሉ ወጣ። በሂደት ማ ከማ ወዴት እንደሚሄድ እናያለን።
ባጭሩ ጠንካራ አስተዳደር ማለት ለራስህ ብቻ የሚመች ስርዓት መገንባት ብቻ ሳይሆን፥ የሰው ልጅ ለሆነ ሁሉ ፦ እንዲሁም ለፍጥረት ሁሉ የሚሆን አስተዳደር መገንባት ይመስለኛል።
አስቤው አላውቅም ነበር። ጠንካራ አስተዳደር ጃንሆይ ላይ አከተመ ነው ምትለኝ?