የመሰንቆ ድምጽ ይመስጠኛል። በገና ይነዝረኛል። ዋሽንት ያረጋጋኛል።
በገጠር የሚኖር አያቴ ስለዋሽንት የነገረኝ ታሪክ እስካሁን ለማመን ይከብደኛል። አያቴ እንደነገረኝ፤ የእረኛን ዋሽንት ለመስማት የሚመጣ ነብር አለ አለኝ። እረኞች ድንገት ረስተውት ዋሽንት ሳይነፉ ከዋሉ፤ ነብሩ ወደሰፈር ዘልቆ ጎጆ ጣራ ላይ ይወጣና፤ የጎጆውን ክዳን ሳር ወደመሬት ነስንሶት ይሄዳል አሉኝ። እረኞቹ ዋሽንት በሚነፉበት ወቅት፤ ዛፍ ላይ ሆኖ ሰምቶ ይሄዳል። ጎጆም አያፈርስም። ሰውም ፈጽሞ ተተናኩሎ አያውቅም አለኝ።
ከነዚህ ባሕላዊ የሚዚቃ መሳሪያዎች፤ በቀላሉ እና በቶሎ ሊለመድ የሚችለው የቱ ነው? በተለይ፤ ከመሰንቆ እና ከዋሽንት?
ቀላል የሚባል ባይኖርም፤ እንደየሰው ቢወሰንም፤ ማሲንቆ የሚከብድ ይመስለኛል።